ኢትዮጵያ,  አፍሪካ

የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለናይል ተፋሰስ ሀገራት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል - ኢንጂነር ጌቱ ቢፍቱ

Author

amc-admin

Date Published

የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለናይል ተፋሰስ ሀገራት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል - ኢንጂነር ጌቱ ቢፍቱ


የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ለናይል ተፋሰስ ሀገራት አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ የውሃ ሀብቶች ከፍተኛ ተመራማሪ ኢንጂነር ጌቱ ቢፍቱ ገለጹ።


በካናዳ አልበርታ ግዛት ተቀማጭነታቸውን ያደረጉት ኢንጂነር ጌቱ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሆነው ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ትልቅ የታሪክ ስኬት ከመሆኑ ባሻገር ለናይል ተፋስስ ሀገራት አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት ነው።


ግድቡ ለኢኮኖሚ እና ለማህበራዊ ጉዳዮች ካለው ትሩፋት ባለፈ፤ በጋራ ልማት እና በፖለቲካዊ ትብብር አማካኝነት የአፍሪካ ቀንድ እና ምስራቅ አፍሪካን የማስተሳሰሪያ ገመድ እንደሆነ ተናግረዋል።



ከፍተኛ ባለሙያው ለተፋሰሱ ሀገራት ህልውና የሆነውን የናይል ወንዝ ዘላቂ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።


በመተማመን እና በመተባበር የውሃ ሀብቱን ለጋራ ብልጽግና መሰረት ወደ ማድረግ ማሸጋገር እንደሚቻልም ነው ከፍተኛ ተመራማሪው የገለጹት።


ግድቡ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ባረጋገጠ መልኩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ስኬታማ በሆነ መልኩ መገንባት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ መሆኑን አመልክተዋል።


ባለሙያው የናይል ተፋሰስ ሀገራት በቁርጠኝነት፣ በትብብር መንፈስ እና በጋራ ራዕይ ቀጣናውን የዘላቂ ልማት እና መረጋጋት ተምሳሌት ለማድረግ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

Related Posts