ዜና,  አፍሪካ

በኬንያ በአቪዬሽን ሰራተኞች ሥራ ማቆም አድማ ምክንያት የአየር ትራንስፖርት ተስተጓጎለ

Author

amc-admin

Date Published

በኬንያ በአቪዬሽን ሰራተኞች ሥራ ማቆም አድማ ምክንያት የአየር ትራንስፖርት ተስተጓጎለ


አሰለፍ ሚዲያ (የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.)፡


በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአቪዬሽን ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ምክንያት ከትናንት ጀምሮ የሀገር ውስጥ እና የውጭ አገር በረራዎች መስተጓጎላቸውን የብዙሐን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡


በሥራ ላይ ደህንነት እና በኢንዱስትሪው ውስጥ በተደረገው ማሻሻያ ምክንያት የስራ ማቆም አድማው መጠራቱ ተገልጿል፡፡ በዚሁም ሳቢያ በርካታ መንገደኞች ከጉዟቸው ተስተጓጉለዋል ተብሏል፡፡


ሁለተኛ ቀኑን በያዘው በዚህ አድማ የአየር ትራፊክ እንቅስቃሴ የቀነሰ ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ ለአራት ሰአታት የሚጠጋ የበረራ መጓተትን አስከትሏል፡፡ ተሳፋሪዎች በመነሻ እና መድረሻ ተርሚናሎች ውስጥ እንዲቆዩ እና አየር መንገዶች በሀገሪቱ የአየር ክልል ውስጥ መርሃ ግብሮችን እንዲያስተካክሉ አስገድዷቸዋል።


አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ መንግስት ከአቪዬሽን ኤጀንሲዎች እና ከዩኒየኖች ጋር እየሰራ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።


የኬንያ አየር መንገድ አብራሪዎች ማህበር የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ሰራተኞችን ጨምሮ የኬንያ አቪዬሽን ሰራተኞች ህብረት አባላት የወሰዱት እርምጃ በአገር አቀፍ ደረጃ የበረራ እንቅስቃሴን በእጅጉ ጎድቷል ብሏል።


ማህበሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ድርጊቱ መጓተትን፣ አቅጣጫ ማስቀየር እና የጉዞ እቅዶችን በማስተጓጎል በአቪዬሽን ዘርፍ ያሉ ባለድርሻ አካላት ላይ ጉዳት አስከትሏል።


"ተጓዦች የጊዜ ሰሌዳ ማስተካከያዎችን እንዲጠብቁ ይመከራሉ" ሲል የኬንያ አየር መንገድ ተጓዦች ወደ አየር ማረፊያ ከመሄዳቸው በፊት የበረራ ሁኔታን እንዲመለከቱ እና መረጃዎችን ከትክክለኛ የመገናኛ ዘዴዎች እንዲከታተሉ አሳስቧል፡፡

Related Posts

ዜና
ኢትዮጵያ
undefined min read

ኤርትራ ተጥሎባት የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን ተከትሎ ሠራዊቷን መልሳ በማጠናከር በአካባቢው በተለይም በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዳይኖር እያደረገች ነው ሲል አንድ የአሜሪካ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሪፖርት አመለከተ።