ዜና,  አፍሪካ

ኬንያ በረመዳን ወቅት በናይሮቢ ሊፈጸም የነበረ የአልሸባብ ጥቃትን አከሸፈች

Author

amc-admin

Date Published

ኬንያ በረመዳን ወቅት በናይሮቢ ሊፈጸም የነበረ የአልሸባብ ጥቃትን አከሸፈች


አሰለፍ ሚዲያ (የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.)፡ - በኬንያ የጸረ ሽብርተኝነት ፖሊስ ይፋዊ መግለጫ የትዊተር ገጽ መረጃ መሰረት የጥቃቱ ሴራ የተቀነባበረው በእስላማዊው ታጣቂ ቡድን አልሸባብ ሲሆን፤ ከወራት ክትትል እና የስለላ ስራዎች በኋላ መክሸፉ ተገልጿል፡፡


በዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ውስጥ በሚንቀሳቀስ ኔትወርክ ላይ ያነጣጠረ ክትትል መደረጉን የገለፁት ባለስልጣናት ከ600 በላይ ጥይቶች፣ ሽጉጦች፣ የእጅ ቦምቦች፣ ፈንጂ ቁሶች እና አደንዛዥ እጾችን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እና ፈንጂዎች መያዙን ገልጸዋል።


ባለሥልጣናቱ አክለውም ቁሳቁሶቹ በናይሮቢ ላሉ ኢላማዎች የታሰቡ ናቸው። ተጠርጣሪዎቹ በረመዳን ወቅት ጥቃት ለማድረስ እቅድ ማውጣታቸው የተነገረ ሲሆን የውጭ ዜጎችን አፈና እና የተሽከርካሪ ጠለፋዎችንም እያጤኑ ነበር ተብሏል።


የኬንያ የጸጥታ ኤጀንሲዎች ናይሮቢ ደህንነቷ የተጠበቀ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውበታል፡፡


ይህም የፖሊስ እና የስለላ መኮንኖች ከፍተኛ ጥረት ታክሎበት ስጋት ያላቸውን ቡድኖች ሌት ተቀን በመከታተል በተደረገ ያላሰለሰ ጥረት መሆኑ ተገልጿል፡፡


መንግስት ከታቀደው ሽብር ጋር ተያይዞ ስለታሰሩ ሰዎች ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫ የሰጠ ሲሆን፥ ምርመራም እየተካሄደ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

Related Posts

ዜና
አፍሪካ
undefined min read

አሰለፍ ሚዲያ (የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም.)፡ - በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአቪዬሽን ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ምክንያት ከትናንት ጀምሮ የሀገር ውስጥ እና የውጭ አገር በረራዎች